አዲስ አበባ አንጸባራቂዋ የአፍሪካ መዲና ናት – ሃስቲንግስ ቺኮኮ

ጥቅምት 27/2015 (ዋልታ) አዲስ አበባ አንጸባራቂዋ የአፍሪካ መዲና ናት ሲሉ የC40 የአፍሪካ ሪጂናል ዳይሬክተር ሃስቲንግስ ቺኮኮ ገለጹ።
አዲስ አበባ እና ከንቲባዋ የC40 አላማዎችን ለማሳካት እያደረጉት ያለው ጥረት የሚደነቅ ነው ነው ያሉት ቺኮኮ፤
ይህ እውቅና የፖለቲካ አመራሩ ቁርጠኝነትና ጉልህ እርምጃ ውጤት ነው ብለዋል፡፡
እንደ አፍሪካዊ ኢትዮጵያዊነታችሁ በተገኘው ሽልማት ካልተደሰታችሁ ምን ያስደስታችሁ ይሆን? ብለው፤
ቆሻሻን መልሶ በመጠቀም ከተማችሁን ከበካይ ጋዝ መታደግ ጀምራችኋል ሲሉም አክለዋል።
አዲስአበባ ከተማ ይህን ታላቅ ዓለም አቀፍ ሽልማት ማሸነፍ የቻለችው ኒውዮርክን ከመሳሰሉ ታላላቅ ከተሞች ጋር ተወዳድራ ነው፤ በዚህም በጣም ደስተኛ ነኝ ማለታቸውን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።