አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው

ሐምሌ 9/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 5 ሺሕ 58 ተማሪዎች አስመረቀ።

ዩኒቨርሲቲው መደበኛ ፣በርቀት በማታ እና በክረምት ያስተማራቸውን ተማሪዎች ነው ያስመረቀው፡፡

ከአጠቃላይ ተመራቂ ተማሪዎች ውስጥ 1 ሺሕ 654 ሴቶች ሲሆኑ 3 ሺሕ 404 ደግሞ ወንድ መሆናቸው ታውቋል።

ዩኒቨርሲቲው በዛሬው እለት ያስመረቀው ለ73ኛ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ጣሰው ወልደሀና (ፕ/ር) ለተመራቂ ተማሪዎች እና ቤተሰቦች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ተመራቂዎች በተመረቁበት የሙያ መስክ ሀገራቸውን በቅንነት እና በታማኝነት እንዲያገለግሉም ጥሪ አቅርበዋል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል፡፡

በአመለወርቅ መኳንንት