አዲስ የተመሰረተው የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ የመጀመሪያ ስብሰባውን አካሄደ

የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ

መጋቢት 5/2014 (ዋልታ) አዲስ የተመሰረተው የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ የመጀመሪያ ስብሰባውን ዛሬ አካሂዷል፡፡

በስበሰባውም የፓርቲው ጉባዔ ያስተላለፋቸው ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች በሚተገበሩበት ሁኔታ ላይ መክሯል፡፡

ማዕከላዊ ኮሚቴው የጉባዔው ውሳኔዎች ተግባራዊ የሚሆኑበት እቅድ ተዘጋጅቶ ውሳኔዎቹና አቅጣጫዎቹ በፍጥነት መተግበር እንዲጀምሩ ውሳኔ ማስተላለፉን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ኮሚቴው በተጨማሪም አዲስ የተገነባውን የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅሕፈት ቤት የመረቀ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄዱ ያሉ ሌሎች የልማት ፕሮጀክቶችንም በመጎብኘት ላይ ይገኛል፡፡