አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ በገዜ ጎፋ ወረዳ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች አጽናኑ

ሐምሌ 17/2016 (አዲስ ዋልታ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፌ ጉባዔ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ ከፍተኛ የፌዴራል መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች አጽናኑ፡፡

በወረዳው ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ ከትናንት በስቲያ በጣለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ የተከሰተው የመሬት መንሸራተት በሰውና በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት ማስከተሉ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ አፈ ጉባዔ ታገሰን ጨምሮ ከፍተኛ የፌዴራል የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች በቦታው ተገኝተው ማጽናናታቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመላክታል፡፡

የክልሉ መንግሥትና የአካባቢው ነዋሪዎች በአሁኑ ወቅት የነፍስ አድንና ተጨማሪ አደጋ እንዳይከሰት ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራትን በርብርብ እያከናወኑ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የሚደረጉ የሰብዓዊ ድጋፍ ሥራዎችም በቅንጅት እየተከናወኑ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡