አፍሪካዊያን የኢትዮጵያን ትግል እንዲቀላቀሉ ምሁራን የመሪነት ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል

ኅዳር 14/2014 (ዋልታ) የአፍሪካ ምሁራን ኢትዮጵያ እያደረገች ያለውን ትግል እንዲቀላቀሉ ኢትዮጵያዊያን ምሁራን የመሪነት ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት ምህረት ደበበ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የአካዳሚው አመራሮችና ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት የደም ልገሳና በተለያዩ አካባቢዎች እገዛ ለሚሹ ዜጎች ድጋፍ አድርገዋል።

የልህቀት አካዳሚው ፕሬዝዳንት በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው የኅልውና ማስከበር ትግል ከዓለም ዐቀፍ ፍላጎቶች ጋር ጭምር ነው።

ጦርነቱ የጠብመንጃ ብቻ ሳይሆን የሐሳብም ጭምር በመሆኑ ምሁራን ይህንን በመመከት ረገድ የማይተካ ሚና እንዳላቸው ተናግረዋል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ ምሁራን ኢትዮጵያ የያዘችውን እውነት ለዓለም በማሳወቅና የአፍሪካ ምሁራንንም በመቀስቀስ የሃሳብ ጦርነቱ አካል እንዲሆኑ በማድረግ አገራዊ ግዴታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ የነፃነት ፋና ወጊ በመሆኗ “ኢትዮጵያን ማንበርከክ ማለት አፍሪካን ማንበርከክ ነው” በሚል እሳቤ ዘመቻ መከፈቱን ጠቅሰዋል፡፡