ኢትዮ ቴሌኮም በመሬት ናዳ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ማድረጊያ አጭር የመልዕክት መላኪያ ቁጥር ይፋ አደረገ

ሐምሌ 17/2016 (አዲስ ዋልታ) ኢትዮ ቴሌኮም ከጎፋ ዞን አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ጋር በመተባበር በጎፋ ዞን በመሬት ናዳ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ማድረጊያ አጭር የመልዕክት መላኪያ ቁጥር ይፋ አደረገ።

ማንኛውም ዜጋ አቅሙ የፈቀደውን የብር መጠን ወደ 8091 በመላክ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖችን መደገፍ እንደሚችልም ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል።

ተቋሙ በገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው ድንገተኛ የመሬት ናዳ ምክንያት የወገኖች ሕይወት በማለፉ የተሰማውን ሀዘንም ገልጿል።