ኢትዮ-ቴሌኮም የ4ጂ የበይነመረብ አገልግሎትን በጋምቤላ ማስጀመር

ነሐሴ 27/2013 (ዋልታ) ኢትዮ-ቴሌኮም በደቡብ ምዕራብ ምዕራብ ሪጅን “የ4 ጂ ኤል ቲ ኢ አድቫንስድ” በይነ መረብ አገልግሎትን አስጀመረ።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ የዛሬውን ጨምሮ በ73 ከተሞች አገልግሎቱን ማዳረስ ተችሏል ብለዋል፡፡

ደንበኞችም አገልግሎቱን ለማግኘት አሁን ከሚጠቀሙበት የ3ጂ የስልክ ቀፎና ሲም ካርድ አጠቃቀም ወደ 4ጂ ቴክኖሎጂ መቀየር እንዳለባቸው ተገልጿል።

(በአመለወርቅ መኳንንት)