ኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለዉን የዉጭ ጫናና ጣልቃ ገብነትን የሚያወግዝ ሰልፍ በኦሮሚያ ሊካሄድ ነው

አቶ አዲሱ አረጋ

ሐምሌ 15/2013 (ዋልታ) – ኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለዉን የዉጭ ጫናና ጣልቃ ገብነትን የሚያወግዝ ሰልፍ በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ከተሞች ሊካሄድ መሆኑን በምክትል ርዕሰ መስተዳዳር ማዕረግ የክልሉ ማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ ገለጹ::

ሰልፉ ኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለዉን የዉጭ ጫናና ጣልቃ ገብነትን ከማውገዝ በተጨማሪ  ለመከላከያ ሰራዊት ያለዉን ድጋፍ ለመግለጽ እንደሚካሄድ ታውቋል::

ሰልፎቹ ከሐምሌ 17/2013 ዓ.ም ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል ባሉ ከተሞች  እንደሚደረጉ አቶ አዲሱ ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የክልሉ ህዝብ ለጀግናዉ የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት ያለዉን አክብሮት እና ድጋፍ ለመግለጽ ሰፋፊ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

“ህዝባችን ለጀግኖቻችን ስንቅ ከማዘጋጀት  ጀምሮ ወጣቶች ከመከላከያ ሰራዊታችን ጎን ተሰልፈዉ  የኢትዮጵያ ጠላቶችን በማሳፈር የአባቶቻዉን ታሪክ እንዲደግሙ መርቆ በመሸኘት ላይ ይገኛል” ሲሉ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት አጭር መልእክት ገልጸዋል፡፡