ኢትዮጵያ በብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ውጤታማ ተሳትፎ አድርጋለች

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ

ሰኔ 13/2016 (አዲስ ዋልታ) ኢትዮጵያ በሶስተኛው የብሪክስ አባል ሀገራት ተወካዮች፣ ውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ያደረገችው ተሳትፎ ውጤታማ እንደነበር ተገለፀ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ በሩሲያ በተካሄደው የብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች መድረክ ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን የሀገሪቱን ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ ውጤታማ ቆይታ ማድረጉን አንስተዋል።

የልዑክ ቡድኑ ከጉባኤው ጎን ለጎን ከ8 ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ፍሬያማ የሁለትዮሽ ውይይት ማድረግም ችሏል።

በተለይ ከሩሲያ፣ ቻይና፣ ብራዚል እና ደቡብ አፍሪካ ጋር የተደረጉት የሁለትዮች ውይይቶች ከሀገራቱ ጋር ያለን ግንኙነት ከማጠናከር ባለፈ ኢትዮጵያ የብሪክስ ልማት ባንክን ለመቀላቀል ያቀረበችው ጥያቄ በፍጥነት ተቀባይነት እንዲያገኝ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ተብሏል።

በአማረ ደገፋው