ኢትዮጵያ አበረታች የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም አድርጋለች

ግንቦት 12/2014 (ዋልታ) የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ ባለፉት ሦስት ዓመታት ኢትዮጵያ አበረታች የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም እያደረገች መሆኑን ገልፀዋል።

የ2014 ዓ.ም በጀት ዓመት የ9 ወራት የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም ሪፖርት ለባለድርሻና የውጭ የኢኮኖሚ አጋር አካላት ቀርቧል።

በሪፖርቱ የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም እንዲሁም የውስጥና የውጭ የኢኮኖሚ ተግዳሮቶች ተዳሰዋል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) የ2014 በጀት ዓመት የ9 ወራት የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም ሪፖርትን ለባለድርሻ አካላት አቅርበዋል፡፡

በመድረኩ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ይናገር ደሴን ጨምሮ ሚኒስትሮች እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በደምሰው በነበሩ