ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በኒውክለር ኢነርጂ ዘርፍ የመግባቢያ ስምምነቶች ተፈራረሙ

ሚያዚያ 08/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር እና የሩሲያው የአቶሚክ ሃይል ኮርፖሬሽን በኒውክለር ኢነርጂ ዘርፍ የመግባቢያ ስምምነቶች ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ በኒውክሌር ሃይል የማህበረሰቡን በጎ ግንዛቤ ለማሳደግዳ እና ስልጠና ለመስጠት እንዲሁም ክህሎት ለማሳደግ የሚያስችል ድጋፍ ለመስጠት ያለመ ነው ተብሏል፡፡

ስምምነቱን በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ እና የሩሲያ የአቶሚክ ሃይል ምክትል ዳይሬክተር ኒኮላይ ስፓስኪ መፈራረማቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡