”ኢትዮጵያ የእኛ እናት” የሚል የሙዚቃ ሥራ ሊቀርብ ነው

ጥር 13/2014 (ዋልታ) ”ኢትዮጵያ የእኛ እናት” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ የሙዚቀኛ ግርማ ይፍራሸዋ ሥራ ለአድማጭ ተመልካች ሊቀርብ ነው።

በተሰማራሁበት የሥራ መስክ ለአገሬ የበኩሌን ለማድረግ ይህንን የሙዚቃ ሥራ አዘጋጅቻለሁ ሲል ፒያኒስት ግርማ ይፍራሸዋ ገልጿል።

ከ50 በላይ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች የተሳተፉበት ይህ ሥራ ዘመን ተሻጋሪ ይሆናል ተብሎም ተስፋ ተጥሎበታል ይጠበቃል።

ፍሬዘር አድማሱ በግጥም እንዲሁም ዳግማዊ ፈይሳ በዝግጅት የተሳተፉበት የሙዚቃ ሥራው ቀጣይ እሁድ በብሔራዊ ቴአትር የሚመረቅ ሲሆን በዝግጅቱ ላይ የሙዚቃ ሥራዎች እና ኪነ ጥበባዊ ዝግጅቶች ይቀርባሉ ተብሏል።

የዝግጅቱ መግቢያ 1 ሺሕ ብር በጦርነቱ ለተጎዱ ወገኖች እንደሚውልም ተገልጿል።