ኢትዮጵያ የገጠማትን ፈተና በድል ትወጣለች – ቲቦር ናዥ

ሐምሌ 29/2013 (ዋልታ) – ኢትዮጵያ ትበተናለች የሚሉ አካላት ተሳሥተዋል ይልቁንም የገጠማትን ፈተና በድል ትወጣዋለች ሲሉ የቀድሞው የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲቦር ናዥ ተናገሩ፡፡

አሁን ላይ የገጠማትን ፈተና በድል ትወጣለች ብለው እንደሚያምኑም ቲቦር ናዥ ገልጸዋል።

ዩጎዝላቪያ የመጀመርያው የዓለም ጦርነትን ባሸነፉ ሀገራት የተፈጠረች መሆኗን ያስታወሱት ቲቦር ናዥ፤ ኢትዮጵያ ግን ከሁለት ሺህ ዓመት በላይ የኖረች ሀገር እንደሆነች በመግለጽ እዚህ የደረሰችውም በርካታ ቀውሶችን ፈትታ አልፋ ነው ብለዋል።

የቀድሞው የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና በኢትዮጵያ የአሜሪካን አምባሳደር የነበሩት ቲቦር ናዥ በቲዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት፤ ኢትዮጵያ እንደዩጎዝላቪያ ትበተናለች የሚሉ ሰዋች ተሳስተዋል ነው ያሉት።

ኢትዮጵያ አሁን ላይ የገጠማትን ፈተና አልፋ ሰላሟን እንደምታረጋግጥና ወድቀድሞ እድገቷ እንደምትመለስም በመልዕክታቸው ገልጸዋል።