ኢትዮጵያ የገጠሟትን ፈተናዎች በማለፍ ድል ማስመዝገቧን ትቀጥላለች – ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

ሐምሌ 23/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያ በቶኪዮ ኦሎምፒክ በ10,000 ሜትር ሩጫ በሰለሞን ባረጋ አማካኝነት የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ በማግኘቷ እንኳን ደስ አለን ብለዋል፡፡

በዚህም ኢትዮጵያ የገጠሟትን ፈተናዎች በማለፍ ድል ማስመዝገቧን ትቀጥላለች ነው ያሉት፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቀሩት ተወዳዳሪዎችም መልካም ዕድል እመኛለሁ ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።