“ኢትዮጵያን ለማዳን አካታች ብሔራዊ ምክክር” በሚል ውይይት ተካሄደ

መጋቢት 21/2014 (ዋልታ) “ኢትዮጵያን ለማዳን አካታች ብሔራዊ ምክክር” በሚል መሪ ሃሳብ የፓናል ውይይት ተካሄደ፡፡
የፓናል ውይይቱን ኢንስቲትዩት ፎር ሴኩሪቲ ስቴዲስ እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምር ኢኒስቲትዩት በጋራ አዘጋጅተዋል።
በፓናል ውይይቱ በኢትዮጵያ የተሳካ አገራዊ ምክክር የማካሄድ አስፈላጊነትና ቅድመ ሁኔታዎች፣ ብሔራዊ ምክክር ከማካሄድ አኳያ ያሉ ዓለም ዐቀፍ ተሞክሮዎችና ታሪካዊ አንድምታ፣ አገራዊ ምክክርን ለማካሄድ የኢትዮጵያ አቅም እና በሌሎች ሃሳቦች ላይ ትኩረት አድርጓል።
የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝምና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ስዩም መስፍን (ዶ/ር) ለረጅም ጊዜያት የቆዩ አገራዊ ችግሮችን በብሔራዊ ምክክር ለመፍታት በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ መንግሥት ሂደቱን ለመደገፍ ቁርጠኛ ነው ብለዋል፡፡
ተሳታፊዎች ለአገራዊ ምክክር ሂደቱ ይበጃል ባሏቸው ሃሳቦች ላይ መምከራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡
ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!