ኢትዮጵያን ከሶማሌላንድ የሚያገናኘው የመንገድ ግንባታ 85 በመቶ ደርሷል

ሐምሌ 5/2014 (ዋልታ) ኢትዮጵያን ከሶማሌላንድ የሚያገናኘው የበርበራ-ቶጎጫሌ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት 85 በመቶ መድረሱን የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክ አገልግሎት ድርጅት አስታውቋል፡፡

የመንገድ ግንባታው በሚጠናቀቅበት ወቅት ኢትዮጵያን ከበርበራ ወደብ በማገናኘት ወጪ ገቢ ንግዱን የሚያሳልጥ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ የበርበራ ወደብን በመጠቀም ኢትዮጵያን ከተቀረው አለም ጋር የሚያገናኝ መውጫ መግቢያ ያደርገዋል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም መንገዱ በኢትዮጵያ እና በሶማሌላንድ መካከል ያለውን የንግድ ምጣኔ በ30 በመቶ ያሳድጋል ነው የተባለው፡፡

በሶስት ምእራፍ እንዲጠናቀቅ የታቀደለትና 234 ኪሎሜትር ርዝመት ያለው የበርበራ-ቶጎጫሌ የመንገድ ግንባታ በፈረንጆቹ 2022 መጨረሻ ላይ እንደሚጠናቀቅ የኢንሳይድ አፍሪካን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።