ኢትዮጵያዊያን እየመረጡ ነው – አልጀዚራ

ሰኔ 14/2013 (ዋልታ) – በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ኢትዮጵያዊያን እየመረጡ መሆናቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።

በርካታ መራጮች በሚገኙባቸው የምርጫ ጣቢያዎች መራጮች ሰልፍ ይዘው ተራቸውን ሲጠባበቁ መታዘቡን አመልክቷል።

አልጀዚራ ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ምርጫው ለኢትዮጵያ ወሳኝ መሆኑን እና የሚመረጠው መንግስት ሰላምን እና አንድነትን ያመጣልናል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ መናገራቸው ተጠቁሟል፡፡

የሰላም ኖቤል ተሸላሚው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ምርጫው ነፃ እና ፍትሃዊ እንደሚሆን መናገራቸውን ዘገባው አስታውሷል።