ኢትዮጵያዊያን የአገር መከላከያ ሰራዊትን እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀረበ

ኅዳር 24/2014 (ዋልታ) መስፈርቱን የሚያሟሉ ኢትዮጵያዊያን የአገርን ኅልውናን ለማስከበር ዋልታና መከታ የሆነውን መከላከያ ሰራዊት እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀረበ፡፡

ኢትዮጵያን ከውስጥ እና ከውጭ ጠላት በመጠበቅ አገራዊ ኅልውናን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና የሚጫዎት ወታደራዊ ተቋም እየተገነባ ነው፡፡

ኢትዮጵያ የገጠማትን ጠላት ወደተመኘው ሲኦል እያወረደች ጎን ለጎን ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ግንባታ ውስጥ ነች፡፡

ኢትዮጵያ እያሸነፈች የመሆኗ ምስጢር በየደረጃው እየተገነባ ያለው የፀጥታ ኃይል በመሆኑ የአገር ግንባታው የማዕዘን ድንጋይ በመሆን የአንበሳውን ድርሻ የሚይዘውን የአገር መከላከያ ሰራዊትን የመቀላቀል ጥሪው የምልመላ መስፈርቱን ለሚያሟሉ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ቀርቧል፡፡

የአገር መከላከያ ሰራዊት ለሕዝብ የቆመ፤ ኢትዮጵያን ያስቀደመ፤ የኢትዮጵያዊያን ውኅድ ማንነት ውጤት የሆነ ታላቅ ተቋም ነው፡፡