ኢትዮጵያዊያን የጀመሩትን ዲፕሎማሲያዊ ትግል ማጠናከር እንዳለባቸው ተገለፀ

ጥር 18/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ አሜሪካዊያን የዜጎች ምክር ቤት ከናቫዳ ግዛት የምክር ቤት አባል (ስናተር) ካትሪን ማሳቶ እና የኮሎራዶ ግዛት የምክር ቤት አባል ጀይሰን ክሮው ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

ሴናተር ካትሪን ማሳቶ በውይይታቸው የኢትዮጵያን ጉዳይ በትኩረት እየተከታተሉ መሆናቸውን ለምክር ቤቱ ተወካዮች አስረድተዋል፡፡

ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ለረጅም ጊዜ የዘለቀ መልካም ግንኙነት እንዳላቸው አንስተው ይህንን ግንኙነት በቀላሉ የምናፈርሰው አይደለም ሲሉ ነው የገለጹት።

በመሆኑም ጉዳዩን በጥልቀት ለመከታተል ዝግጁ መሆናቸውን በማረጋገጥ ኢትዮጵያዊያን በአንድነት ሆነው የጀመሩትን የዲፕሎማሲ ጥረት መግፋት እንዳለባቸው መክረዋል።

በተያየዘ ኮንግረስማን ጀይሰ ክሮው የጆ ባይደን አስተዳደር አጎዋን በመጠቀም ሕወሓትን ለመደገፍ የወሰደው እርምጃ የኢትዮጵያን ሕዝብ የሚጎዳ እንደሆነ ነው የጠቆሙት፡፡

ለሰብዓዊ እርዳታ ተብለው የተዘረጉ ፕሮጀክቶችን ለፖለቲካዊ ጥቅም ማዋል አሜሪካዊ ባህሪ አይደለም ሲሉም ለምክር ቤቱ ተወካዮች ገልጸዋል፡፡

ከኢትዮጵያ አሜሪካዊያን የዜጎች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመላክተው ሴናተር ጀይሰን ክሮው የአጎዋን ጉዳይ እንደሚያውቁና ጉዳዩን በቅርበት እንደሚከታተሉት ገልጸዋል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://www.facebook.com/waltainfo
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!