ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን በስዊዘርላንድ ጄኔቫ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ

ኅዳር 17/2014 (ዋልታ) በስዊስዘርላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያን የአንዳንድ አሜሪካ መር ምዕራባዊያን አገራትን በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብነት በመቃወም በጄኔቫ ሰልፍ አካሄዱ፡፡

ሰልፈኞቹ ዓለም ዐቀፍ መገናኛ ብዙኃን ኢትዮጵያን በተመለከተ የሚያሰራጯቸውን የሀሰት ዘገባዎችም አውግዘዋል፡፡

ጄኔቫ የተባበሩት መንግሥታት የተለያዩ ኤጀንሲዎችን ጨምሮ በርከት ያሉ ዓለም ዐቀፍ ተቋማት የሚገኙባት ትልቋ የዲፕሎማሲ ማዕከል መሆኗ ይታወቃል።