ኢንስቲትዩቱ 400 የኢትዮጵያ ደረጃዎችን አፀደቀ

ሰኔ 17/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ደረጃ ኢንስቲትዩት 400 የኢትዮጵያ ደረጃዎችን አፀደቀ።
የፀደቁት የምርትና አገልግሎት ደረጃዎች አስመልክቶ ኢንስቲትዩቱ መግለጫ እየሰጠ ይገኛል።
ደረጃዎቹ በምግብና በእርሻ በአካባቢ ጤና፣ በኬሚካልና ኬሚካል ውጤቶች፣ በኤሌክትሮ መካኒካል እንዲሁም በኮንስትራክሽን እና ሲቪል ኢንጅነሪንግ ዘርፎች የተዘጋጁ ናቸው ተብሏል።
በየዘርፎቹ የፀደቁት ደረጃዎች ከኅብረተሰቡ ጤናና ደኅንነት፣ አካባቢ ጥበቃ እና የሸማቾችን ጥቅም ከማስጠበቅ አኳያ ሚናቸው የጎላ ነው ተብሏል።
በሱራፌል መንግስቴ