ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ

ኅዳር 14/2014 (ዋልታ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾን (ዶ/ር) ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ መረጠ፡፡

የክልል ምክር ቤቱ በመጀመሪያ ጉባኤው የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ያስመረጠ ሲሆን በክልሉ ህገ መንግስት አንቀፅ 73 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት  በኢፌዴሪ ውሃ እና ሀብት ሚኒስትር  ዴኤታ የነበሩትን ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾን (ዶ/ር) በ51 ድምፅ እና በአንድ ድምፀ ተዓቅቦ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾመዋል፡፡

ምስረታውን በዛሬው እለት እያደረገ የሚገኘው የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል  የሚተዳደርበትን 11 ምዕራፎች እንዲሁም 123 አንቀፆች ያሉበትን ህገ መንግስት ያጸደቀ ሲሆን የክልሉ ምክር ቤት አፌ ጉባኤና ምክትል አፈ ጉባኤ መምረጡ ታውቋል።