የካቲት 13/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) የተግባቦት መሠረታዊ ሀሳብና ሀገራዊ ምክክር ፋይዳ እንዲሁም ዓለም ዐቀፋዊ ተሞክሮ በሚል ሀሳብ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር እያደረገ ይገኛል።
በሀገራዊ ምክክሩ ላይ ኢዜማ ኢትዮጵያን ለማሻገር በሚደረገው ጥረት አስተዋፅኦን ለማበርከት ዝግጁ እንደሆነ የተናገሩት የፓርቲው ምክትል መሪ አንዱአለም አራጌ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሀገርን በሚመጥን መልኩ ለምክክሩ መዘጋጀት እንዳለበት ተናግረዋል።
መንግሥትና የፖለቲካ ፓርቲዎችም ለሀገራዊ ምክክሩ በቂ ዝግጅት በማድረግ ኢትዮጵያን ለማሻገር ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው ገልፀዋል።
ምክክሩ ውጤት እንዲያመጣም በትኩረት መሰራት እንዳለበት የኢዜማ ምክትል መሪው ጠቁመዋል።
በሱራፌል መንግሥቴ