ኢጋድ 2ኛውን ዓለም ዓቀፍ ሳይንሳዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው

 

የኢጋድ አባል ሀገራት

የካቲት 15/2013 (ዋልታ) – ኢጋድ ስደትንና መፈናቀልን በተመለከተ 2ኛውን መደበኛ ሳይንሳዊ ስብሰባ እያካሄደ ይገኛል::

የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) አባል ሀገራት ርዕሳነ ብሔራት እና ርዕሳነ መንግሥታት ስደትና መፈናቀልን በተመለከተ 2ኛውን መደበኛ ሳይንሳዊ ስብሰባ እያካሄደ ይገኛል፡፡

በስብሰባው መክፈቻ የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ እንደተናገሩት አባል ሀገራቱ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቀውስ አያያዝና ግጭቶችን በማስቀረት ረገድ ለውጦች አሳይተዋል ሲሉ ገልፀዋል። በእነዚህ ጥረቶች ስደትና መፈናቀሎች በቀጠናው ከማስቀረት አኳያ ስኬታማ ውጤቶች ታይቷል ሲሉም አክለዋል፡፡

በምስራቅ አፍሪካ ስደትና መፈናቀሎች መኖር ምክንያትና መፍትሔዎቹን የሚያመላክቱ ሳይንሳዊ የጥናት ጽሑፎችም እየቀረቡ ይገኛሉ።

ቀጠናው በተደጋጋሚ ድርቅ የሚያጠቃው፣ ተለዋዋጭ የዝናብ መጠን ያለው፣ ግጭት የበዛበት ፣ደካማ ተቋማት ያሉበት፣ ከፍተኛ የስራ አጥ ቁጥር የሚታይበት፣ ድህነት እና ዝቅተኛ የጤና አግልግሎትን የሚያስትናግድ በግብርና እና በቁም እንስሳት ሃብት ላይ ጥገኛ እንደሆነም በጽሑፎቹ ተብራርቷል።
(በደረሰ አማረ)