ኢጋድ መንግሥት የሰሜኑን ግጭት ለመፍታት ሁሉን ዐቀፍ ውይይት ለማድረግ መወሰኑን ደገፈ

ሰኔ 28/2014 (ዋልታ) የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) የኢትዮጵያ መንግሥት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሁሉን ዐቀፍ ውይይት ለማድረግ የወሰደውን አዎንታዊ እርምጃ እንደሚደግፍ አስታወቀ፡፡

መንግሥት በሰብአዊ አቅርቦት ዙሪያ እየሰራ ያለውንም ሥራ ማድነቁን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኬንያ ናይሮቢ የተካሄደው 39ኛው የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) አባል ሀገራት ርዕሳነ ብሔራት እና መሪዎች ጉባኤ ልዩ ልዩ የጋራ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል፡፡