ኢጋድ አባል አገራት መሪዎች ኢትዮጵያ ለወሰደችው ሕግ የማስከበር ተግባር ሕጋዊነት እውቅና በመስጠታቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አመሰገኑ

የኢጋድ አባል አገራት መሪዎች ኢትዮጵያ ለወሰደችው ሕግ የማስከበር ተግባር ሕጋዊነት በመረዳታቸው እና እውቅና በመስጠታቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አመሰገኑ።

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ኢጋድ 38ኛ አስቸኳይ የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ በጅቡቲ ተካሂዷል።

በዚህ ጉባኤም የኢጋድ አባል አገራት መሪዎች ኢትዮጵያን ለመደገፍ ያላቸውን ቁርጠኝነት መግለፃቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ገፃቸው አስታውቀዋል።