ኤጀንሲው የአገርን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ጊዜውን የዋጁ ሥራዎችን አጠናክሮ ይቀጥላል – ሹመቴ ግዛው (ዶ/ር)


ጥቅምት 30/2014 (ዋልታ) – ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የአገርን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ጊዜውን የዋጁ ሥራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ሹመቴ ግዛው (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ዶ/ር ሹመቴ  ሁለተኛውን የሳይበር ደህንነት ወር ሲከበር የተሳካ እንደነበረ ወሩን ማጠናቀቅያን ምክንያት በማድረግ በሰጡትጋዜጣዊ መግለጫ የአገሪቷን የሳይበር ደህንነት ጥቃት መከላከል እና ምህዳሩን ማስጠበቅ የሁሉም ሀላፊነት ነው፤ ሁሉም በጋራ መስራት እንዳለበት ብለዋል፡፡

በዘርፉ የህብረተሰቡን ንቃተ ህሊና፣ የተቋማት ተሳትፎ እና ግንዛቤን ማሳደግ እንዲሁም  የሳይበር ደህንነት ማስጠበቅ የሁሉም በመሆኑ ቅንጅታዊ አሰራር ላይ ትኩረት መደረጉ ተገልጿል፡፡

በሳይበር ደህንነት ወር ጥናታዊ ጽሑፎች፣ አውደርዕይ እና ውይይቶች ተካሂዷል።
(በሚልኪያስ አዱኛ)