“እመርጣለሁ፤ አረንጓዴ አሻራዬን አኖራለሁ ” በሚል ለሚከናወነው የችግኝ ተከላ ከ2.8 ሚሊየን በላይ ችግኞች ተዘጋጅተዋል

ሰኔ 11/2013 (ዋልታ) – የአዲሰ አበባ ከተማ የተፋሰስና አረንጓዴ አካባቢዎች ልማት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር  ኢንጂነር ጽዮን ተሾመ “እመርጣለሁ አሻራዬን አኖራለሁ “በሚል  ለሚከናወነው የችግኝ ተከላ መርሐግብር ከ2.8 ሚሊዮን በላይ  ችግኞች እና ጉድጓዶች ከወዲሁ ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ፡፡

የፊታችን ሰኞ በሚካሄደው 6ኛው ሀገራዊ  ምርጫ ከአረንጓዴ ልማት ጋር በማቀናጀት ህብረተሰቡም ከምርጫው ጎን ለጎን  የአረንጓዴ አሻራውን ማኖር እንዳለበት የገለጹት ዋና ዳይሬክተሯ በአዲስ አበባ በሚደረገው ኢትዮጵያን እናልብሳት የችግኝ ተከላ  መርሐግብር  ተሳታፊ ብቻ ሳይሆን ባለቤት መሆን አለበት ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ  ከተማ ደረጃ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ከ7.5 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለመትከል ዕቅድ መያዙን   ኃላፊዋ ጠቁመዋል

ሕብረተሰቡም  ለሀገሩ ያለውን ክብር እና ፍቅር ችግኝ በመትከል በተግባር እንዲያረጋግጥ ጥሪያቸውን ማቅረባቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡