ግንቦት 6/2014 (ዋልታ) በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ “እኔ ለከተማዬ ፅዳትና ውበት ባለቤት ነኝ” በሚል መሪ ሀሳብ የፅዳት ዘመቻ ተካሂዷል፡፡
በፅዳት ዘመቻው የተገኙት የክፍለ ከተማው የፅዳት አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ኃለፊ አሸናፊ ተፈሪ አካባቢን ማፅዳት ለሀገር ውበት እና የቤተሰብ ጤንነትን ለማስጠበቅ ወሳኝ በመሆኑ የዘወትር ተግባር ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡
ከተማዋን ውብና ማራኪ ለማድረግ ሀሉም ኅብረተሰብ ፅዳትን ከቤቱ እና ከአካባቢው መጀመር እንዳለበትም ገልጸዋል፡፡
በፅዳት ዘመቻው የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጀማል ረዲን፣ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች እና በርካታ ቁጥር ያላቸው የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ተሳትፈዋል፡፡
በአመለወርቅ መኳንንት
ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!