እየጨመረ የመጣውን የዘይት ዋጋ ለማረጋጋት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

መጋቢት 7/2014 (ዋልታ) መንግሥት እየጨመረ የመጣውን የምግብ ዘይት ዋጋ ለማረጋጋት እየሰራ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
12 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሊትር ዘይት በአስቸኳይ ሁኔታ አገር ውስጥ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን የገለጹት የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ ከዚህም ውስጥ 4 ነጥብ 8 ሚሊየን ሊትሩ መግባቱን ተናግረዋል፡፡
ቀሪው 7 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሊትር ደግሞ በቀጣይ እንደሚገባ እና ለ3 ወራት ያህል በየወሩ 50 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት ውሳኔ ላይ መደረሱን ገልፀዋል።
በተስፋዬ አባተ