ኦባሳንጆ በኢትዮጵያ ያለውን የሰላም ሂደት አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጡ

ሐምሌ 29/2014 (ዋልታ) ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ በኢትዮጵያ ያለውን የሰላም ሂደት አስመልክቶ ለአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና ደህንነት ካውንስል ማብራሪያ ሰጡ፡፡

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ ችግሩን በሰላም ለመፍታት ይቻል ዘንድ የአፍሪካ ሕብረት በልዩ መልዕክተኝነት የመደባቸው የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ አንዴ አዲስ አበባ ሌላ ጊዜ ደግሞ መቀሌ እየተመላለሱ ከሁለቱም ወገኖች ጋር ውይይት ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡

ይህን ተከትሎም በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ያለውን ችግር በተመለከተ ያለውን መሻሻል በሪፖርታቸው አመልከልተዋል፡፡

የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና ደህንነት ካውንስል በልዩ መልዕክተኛው የተደረገለትን ማብራሪያ አድንቆ ሕብረቱ እና አጋር አካላት ለተጀመረው የሰላም ጥረት ስኬት ተገቢውን ድጋፍ እንዲያርጉ ጥሪ ማቅረቡን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡