ከ1 ሺሕ በላይ ወጣቶች የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል ሰበሰቡ

ኅዳር 23/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስተባባሪነት ከየክፍለ ከተማው የተውጣጡ ከአንድ ሺሕ በላይ ወጣቶች የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል በመሰብሰብ ደጀንነታቸውን አሳዩ።

በአቃቂ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 የሰባት ዘማች ቤተሰቦች 15 ሄክታር ሰብል ነው የተሰበሰበው።

የአገር ሉኣላዊነትን ለማስከበር ልጆቻቸውን ወደ ግንባር የላኩ ቤተሰቦችን ሰብል በመሰብሰብ ዘምተናል ሲሉም ወጣቶቹ ተናግረዋል።

‹‹በግንባር አሸባሪው ሕወሓት ይታጨዳል በማሳ ደግሞ እህል ›› ያሉት ወጣቶቹ ሁሉም በያለበት ዘማች ነው ብለዋል።

ወጣቶቹ ለዘማች ቤተሰቦች ድጋፋችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በትእግስት ዘላለም