ሰኔ 07/2013 (ዋልታ) – ከ50ሺህ በላይ ወጣቶች የተሳተፉበት የብልፅግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ በአዲስ አበባ ስታዲየም ተካሄደ።
በመርኃግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ብልጽግና ለመጭው ትውልድ ወንድማማችነት እና አብሮነትን እንጂ ጥላቻን አያወርስም ብለዋል።
ብልፅግና ቃሉን ይጠብቃል፤ ይተገብራል ያሉት ምክትል ከንቲባዋ፣ በሰልፉ ለተገኙ ወጣቶች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ አለሙ በበኩላቸው፣ ብልፅግና እውን እንዲሆን የወጣቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በድጋፍ ሰልፉ ላይ የብልጽግና ፓርቲን ወክለው ለህዝብ ተወካዮች እና ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የሚወዳደሩ እጩዎች ስታዲየሙን በመዞር ከወጣቶቹ ጋር ትውውቅ አድርገዋል።
(በሳራ ስዩም)