በገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ ግምታዊ ዋጋቸው 75 ሚሊየን 574 ሺህ 275 ብር የሚገመት ዕቃ ከታህሳስ 9 እስከ 15 ቀን 2013 ዓ.ም ባለው አንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ተይዟል፡፡
ከዚህ ውስጥ ወደ ሀገር ለማስገባት ሲሞከር የተያዘው 63 ሚሊየን 704 ሺህ 085 ብር ግምታዊ ዋጋ ያለው ሲሆን የተቀረው ደግሞ ከሀገር ሊወጣ ሲል የተያዘ ነው፡፡
በተጠቀሰው ጊዜ ከተያዘው የኮንትሮባንድ እቃ ውስጥ ከሀገር ሊወጣ የነበረ 312 ኩንታል ቡና፣ የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች፣ አደንዛዥ እፆች፣ መድኃኒቶች፣ የጦር መሳሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮስሞቲክስ፣ የመለዋወጫ እቃዎች፣ የተለያዩ አልባሳት እና የቀንድ ከብቶች ይገኙበታል፡፡
እቃዎቹን ሲያጓጉዙ የነበሩ 19 ተጠርጣሪ ግለሰቦች ደግሞ በህግ ቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ የተያዙት በፍተሻ፣ በብርበራ እና በተሽከርካሪ በመከታተል ሲሆን የጉምሩክ ሰራተኞች እና አመራሮች ከፌደራል እና ክልል ፖሊስ አባላት ጋር በቅንጅት በመስራት እነዚህን የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ለማዋል ተችሏል፡፡
(ምንጭ፡- የገቢዎች ሚኒስቴር )