ከ773 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት 97 ኪ.ግ ኮኬይን ቦሌ ኤርፖርት ተያዘ

ኮኬይን የተባለ አደንዛዥ እፅ

መስከረም 18/2015 (ዋልታ) ከ773 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት 97 ኪ.ግ ኮኬይን የተባለ አደንዛዥ እፅ በአዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት በቁጥጥር ሥር መዋሉን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ።

መነሻዋን ከናይሮቢ ኬንያ መዳረሻዋን አዲስ አበባ ያደረገች ግለሰብ 97.48 ኪሎ ግራም የሚመዝን ኮኬይን በሁለት ሻንጣዎች ይዛ ለማሳለፍ ስትሞክር በጉምሩክ ኮሚሽን ኤርፖርት ቅርንጫፍ በቁጥጥር ሥር ውላለች።

ተጠርጣሪዋ የትራንዚት መንገደኞች እና ቀረጥ እና ታክስ የሚከፈልበትን ዕቃ ያልያዙ መንገደኞች የሚወጡበትን በዝቅተኛ የስጋት ደረጃ ወይም አረንጓዴ የጉምሩክ ማለፊያ መስመር (Green Line) በመጠቀም እያንዳንዳቸው 48.62 እና 48.86 ኪሎግራም ክብደት ያላቸውን ሁለት ሻንጣዎችን ለማሳለፍ ስትሞክር መያዟን ኮሚሽኑ አስታውቋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW