ከሕገወጦች የተያዘ ዘይት ለኅብረተሰቡ ተከፋፈለ

ሚያዝያ 2/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በከተማዋ በተለያዩ ጊዜያት በተደረገ የቁጥጥር ሥራ ከሕገወጦች የተያዘው ከ750 ሺሕ ሊትር በላይ ዘይት ለኅብረተሰቡ መከፋፈሉን ገለጸ።

የቢሮው ኃላፊ አደም ኑሪ ሕገወጥ ነጋዴዎቹ ዘይቱ የተወረሰባቸው ገበያው እየፈለገው በሚፈለገው ፍጥነት ወደ ገበያ ባለማቅረባቸው ነው ብለዋል፡፡

አክለውም የዘይት ምርቱ አዲስ አበባ ከተማ ገበያ መቅረብ እያለበት ወደ ተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ሲጭኑ በመገኘታቸው መሆኑን ገልጸዋል ሲል ኢፕድ ዘግቧል፡፡