ከሳዑዲ አረቢያ 1 ሺህ 777 ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው ተመለሱ፣

ሰኔ 22/2013 (ዋልታ) – በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የተቀናጀ ጥረት በመደረግ ላይ እንደሚገኝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽ/ቤት አስታውቋል።

በዚህ መሰረትም በትናትናው ዕለት 1 ሺህ 777 ዜጎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉ ተገልጿል።