ከሳዑዲ አረቢያ 441 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመለሱ

ኅዳር 6/2014 (ዋልታ) በሳውዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ አገራቸው ለመመለስ እየተደረገ ባለው ጥረት 108 ህጻናትን ጨምሮ 441 ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ጂዳ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።
በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል ተወካይ ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ አቀባበል ማድረጋቸውን ከሚኒስቴሩ ቃልአቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።