ከሳዑዲ አረቢያ በ3ኛው ዙር በረራ 370 ዜጎች ተመለሱ

ከሳዑዲ አረቢያ ተመላሾች

ሚያዝያ 10/2014 (ዋልታ) ከሳዑዲ አረቢያ ጂዳ ዛሬ በተደረገው ሦስተኛው በረራ 370 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

ከተመላሾች መካከል 247ቱ ሴቶች፣ 94ቱ ህጻናት እና 29 ወንዶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ተመላሾች አዲስ አበባ ሲገቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰራተኞች አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

በዛሬው ዕለት በመጀመሪያው ዙር በረራ 348 ዜጎች በሁለተኛው ዙር በረራ ደግሞ 354 ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ መመለሳቸውን መዘገባችን ይታወቃል፡፡

መንግሥት በሳዑዲ አረቢያ በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ 102 ሺሕ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ብሔራዊ ኮሚቴ በማዋቀር ወደ ሥራ መግባቱ ይታወሳል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW