ከሳዑዲ ዓረቢያ 1 ሺሕ 148 ኢትዮጵያዊያን ተመለሱ

ከሳዑዲ ዓረቢያ የተመለሱ ዜጎች

ሚያዝያ 21/2014 (ዋልታ) በሳዑዲ ዓረቢያ ችግር ውስጥ የነበሩ 1ሺሕ 148 ኢትዮጵያዊያን በዛሬው ዕለት ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ከተመላሾቹ መካከል 12ቱ ህጻናት ሲሆኑ 1ሺሕ 136 የሚሆኑት ደግሞ ወንዶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ መደረጉንም ከሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

እስካሁን ድረስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ሥራ ቁጥራቸው ከ16 ሺሕ በላይ ኢትዮጵያዊያንን መመለስ መቻሉ ተመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW