ከተማ አስተዳደሩ ለመከላከያ ሰራዊት ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

ጥቅምት 3/2015 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት ከ30 ሚሊየን 249 ሺሕ 978 ብር በላይ ድጋፍ አደረገ፡፡

ከተማ አስተዳደሩ ያደረገው ድጋፍ ለ4ኛ ዙር ሲሆን ሁሉንም ክፍለ ከተሞችን በማሳተፍ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

በዚህም 477 ሰንጋዎች፣ 319 ኩንታል ደረቅ ምግብ፣ 2 ሺሕ 30 ዘይት፣ ፍራሽ፣ አልባሳት እና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስን ጨምሮ ሌሎች ለሰራዊቱ የሚውሉ ድጋፎችን በማሰባሰብ አስረክቧል።

ድጋፉን ያስረከቡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ሙሉጌታ ተፈራ አስተዳደሩ ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ሲያደርግ ለ4ኛ ጊዜ ሲሆን በመጀመሪያ፣ በ2ኛ እና 3ኛ ዙር ከ214 ሚሊየን 364 ሺሕ 943 ብር በላይ የሚገምት የዓይነት ድጋፍ ማድረጉን አስታውሰዋል።

ድጋፋን የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች ከከተማው መስተዳድር ጋር በጋራ አስረክበውታል።

በከንቲባ ማዕረግ የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ነጂባ አክመል የመከላከያ ሰራዊቱ የኢትዮጵያን ኅልውና ለማስጠበቅና አሸባሪው ቡድን የከፈተውን ጦርንት ለመቀልበስ በሚያደርገው ተጋድሎ በስንቅና በሞራል በመደገፍ ደጀንነታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የመከላከየያ ሚኒስተር ዴኤታ ማርታ ሎጂ አስተዳደሩ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

የተፎካካሪ ፓርቲ የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ሙልጌታ አበበ በበኩላቸው ሁለት ሀሳብ እንጂ ሁለት ሀገር የለንም፤ ሀገርን ለሚጠብቀው ሰራዊታችን ድጋፋችንን አጠናክረን እቀጥላለን ብለዋል፡፡

በብሩክዊት አፈሩ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW