ከንቲባ አዳነች በ60 ቀናት በተገነቡ ቤቶች ተጠቃሚ ለሆኑ ዜጎች ሥጦታ አበረከቱ

ነሐሴ 10/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በልደታ ክፍለ ከተማ ጌጃ ሰፈር አካባቢ በ60 ቀናት በተገነቡ ቤቶች ተጠቃሚ ለሆኑ ዜጎች የአልባሳትና የበግ ስጦታ አበረከቱ፡፡

ከንቲባዋ አንድነትን በማጠናከር እርስ በእርስ መደጋገፍ እንደሚገባ እና ሰርካዊ ግንኙነትን ወደ ማኅበር ማሳደግ ይገባል ማለታቸውን የክፍለ ከተማው መረጃ ያመለክታል፡፡

ይህ ሲሆን ፍቅርና ተድላ የሰፈነበት ጉርብትናን ማዳበር ያስችላል ነው ያሉት፡፡