ከንቲባ አዳነች በብራዚል ቆይታቸው ከተለያዩ ከተሞች ከንቲባዎች ጋር ተወያዩ

ጥቅምት 9/2015 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በ8ኛው የMUFPP (Milan Urban Food Policy Pact) ግሎባል ፎረም ለመሳተፍ በብራዚል ከነበራቸው ቆይታ ጎን ለጎን ከተለያዩ ከተሞች ከንቲባዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በዚህም ከሪዮ ዴጄኔሮ ከንቲባ ኤድዋርዶ ዳኮስታ፤ ከሚላን ከተማ ምክትል ከንቲባና የሚላን የምግብ ተስማሚነት ፖሊሲ ሃላፊ አና ስካቩዞ እንዲሁም ከፓሪስ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኦድሬ ፑልቫር ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል፡፡

በውይይቶቹም በከተሞቹም መሃከል የሁለትዮሽ ጠንካራ ግንኙነት የመመስረትና ቀጣይ ትብብርን የሚያጠናክሩ አለፍ ሲልም የእህትማማች ከተማነት ግንኙነትን ለመጀመር የሚያስችሉ ምክክሮች  መደረጋቸውን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

በ8ኛው የMUFPP ግሎባል ፎረም ላይ አዲስ አበባ ‘በትምህርት ቤቶች የምገባ ፕሮግራም’ ምርጥ ተሞክሮ ዘላቂ አመጋገብ እና ስነ-ምግብ ዘርፍ በአለም አቀፍ ደረጃ በተደረገ ውድድር አሸናፊ መሆኗ ይታወቃል።