ከንቲባ አዳነች አቤቤ የገርጂ መኖሪያ መንደርን ጎበኙ

ሰኔ 3/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ያስገነባውን የገርጂ መኖሪያ መንደርን ጎበኙ፡፡

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ያስገነባው የገርጂ መኖሪያ መንደር የፊታችን እሁድ የሚመረቅ ሲሆን ግንባታውም በ18 ወራት መጠናቀቁ ተገልጿል፡፡

ከንቲባዋ በጉብኝታቸው በአጭር ጊዜ እንደዚህ ዓይነት ግዙፍ ፕሮጀክት በከተማችን መሰራቱ ለከተማው ውበት እና እድገት ትልቅ ነገር ነው ብለዋል፡፡

በእንዲህ አይነት ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የከተማውን የቤት ችግር ለመፍታት የሚንቀሳቀሱ አልሚዎችን የከተማ አስተዳደሩ እንደሚያበረታታም መግለፃቸውን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW