ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፖሊስነት የራስን ህይወት ለሌሎች አሳልፎ መስጠት ነው አሉ

ግንቦት 13/2014 (ዋልታ) ፖሊስነት የራስን ህይወት ለሌሎች አሳልፎ መስጠት ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ።

ከንቲባዋ ይህንን ያሉት የአዲስ አበባ ፖሊስ ያሰለጠናቸውን ምልምል ፖሊሶች ባስመረቁበት ወቅት ነው።

ከንቲባዋ ሀገሪቱ የኅልውና ጥያቄ ውስጥ በገባችበት ወቅት በከተማዋ የሽብር ተግባር ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አካላትን ተግባር ማክሸፍ መቻሉን አስታውቀዋል።

የፖሊስ አባላት በከተማዋ ላይ እየተስተዋሉ ያሉትን ወንጀሎች በመከላከል የሕዝብን አደራ ሊወጣ ይገባልም ብለዋል።

በዙፋን አምባቸው

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW