ከንቲባዋ ለ1443ኛው የኢድ አል-አደሃ ዐረፋ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ሐምሌ 1/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤበ ለመላው እስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ለ1443ኛው የኢድ አል-አደሃ ዐረፋ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

በዓሉን ስናከብር መልካም እሴቶቻችንን በማጠናከርና የተቸገሩ ወገኖቻችንን በመርዳት ሊሆን ይገባል ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ከንቲባዋ የሰላማችን ዋልታ የሆነውን አብሮነታችንን እና ወንድማማችነታችንን በማጠናከር እንዲሆን እመኛለሁ ሲሉም ነው የገለጹት፡፡