ከንቲባዋ በሕክምና ላይ የሚገኙትን ፓትርያርክ ጎበኙ

የካቲት 21/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሕክምና ላይ የሚገኙትን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያን ሆስፒታል ሄደው ጎበኙ፡፡

በዙሪያቸው እንክብካቤ እያደረጉላቸው ያሉትን የህክምና ባለሙያዎችና አባቶች ምስጋና እንደሚገባቸው ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

ከንቲባዋ “ፈጣሪ በምህረቱና በቸርነቱ ይፈውሳቸው ዘንድ ከልብ እመኛለሁ” ሲሉም ገልጸዋል፡፡