ከንቲባዋ በቂርቆስና ልደታ ክፍለ ከተሞች እየተከናወኑ ያሉ የ60 ቀናት ፕሮጀክቶችን አፈፃፀም ጎበኙ

ሰኔ 4/2014 (ዋልታ) ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቂርቆስና ልደታ ክፍለ ከተሞች እየተከናወኑ ያሉ የ60 ቀናት ፕሮጀክቶችን አፈፃፀም ተዘዋውረው ጎበኙ።

ከንቲባዋ በክፍለ ከተሞቹ  በልዩ ሁኔታ የሚተገበረውን ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች  በየጊዜው በቅርበት አየተከታተሉ ይገኛሉ።

ከንቲባዋ በጉብኝታቸው ወቅት እንደገለፁት፥ ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸው እቅድ መሰረት እየተከናወኑ መሆኑን ገልፀው ፕሮጀክቶች በወቅቱ እንዲጠናቀቁም የክትትልና ቁጥጥር ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

በአሁን ሰአት በእነዚህ ክፍል ከተሞች እየተከናወኑ ያሉ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ሌት ከቀን እየተሰራ እንደሚገኝ ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።