ከንቲባዋ የህፃናትና ወጣቶች ቲያትር ህንፃ ግንባታ እና የሀገር ፍቅር ትያትር ቤትን ጎበኙ

ሰኔ 20/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ እየተገነባ የሚገኘውን የአዲስ አበባ ህፃናትና ወጣቶች ቲያትር ህንፃ ግንባታ እና የሀገር ፍቅር ትያትር ቤትን ጎበኙ።

ወጣቱ ትውልድን ለመግንባት የባህል ማዕከል ያስፈልጋል ያሉት ከንቲባዋ ይህንንም ለማድረግ ትውልድ ሚቀርፅበት እና ኢትዮጵያዊነት የሚጎለትበት ቤት እንድሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

በዚህም የከተማ አስተዳደሩ የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ መሆኑን የገልፁ ሲሆን ትውልድን በኢትዮጵያዊነት ለማነፅ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የሀግር ፍቅር ትያትር ቤት በቅርቡ እድሳት የተደረገለት ሲሆን ለጥበበኞች ክፍት በመሆን እያገለገለ ይገኛል፡፡

በእመቤት ንጉሴ