ከአማራ ክልል መንግሥት የተላለፈ ጥሪ

ነሐሴ 30/2013 (ዋልታ) የአማራ ክልላዊ መንግሥት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ሕዝባዊ ጥሪ አስተላለፈ።
ክልሉ ባቀረበው ጥሪ አሸባሪው ሕወሓት እየሸሸ መሆኑን ጠቅሶ የዘረፈውን የመንግሥትና የሕዝብ ሃብት ይዞ እንዳይወጣ ሕዝቡ የተደራጀ እርምጃ እንዲወስድ ነው የጠየቀው።
ከአማራ ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው የመግለጫው ሙሉ ቃል ቀጥሎ ቀርቧል
በሁሉም የህልውና ዘመቻ ግንባር አካባቢ ላለው ህዝባችን፤ አሸባሪው የትህነግ ቡድን በሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ በልዩ ኀይል፣ በሚሊሻ፤ ፋኖ እና በመላው ሕዝባችን እየተወሰደበት ባለው ከባድ ምት እና እርምጃ ጠላት እየተበታተነ ይገኛል፡፡
ስለሆነም የሕዝብ ጠላት የሆነው የአሸባሪው እና ወራሪው ትህነግ ቡድን የዘረፈውን የሕዝብ እና የመንግሥት ሃብት ይዞ እንዳይወጣ በየአካባቢው ተደራጅተህ እርምጃ እንድትውሰድ የክልሉ መንግሥት ጥሪ ያቀርባል።
በተለይም በመርሳ ግምባር ሚሌና ጊራና አካባቢ፣ ከመርኮታ ወደ ፋጂ የባቡር መስመሩን ተከትሎ፣ ከጎኃ ጀምሮ ወደ ሚሌ አቅጣጫ፣ በመቄት ግምባር ከገረገራ ጀምሮ እስከ ድልብ ደረስ፣ በላስታ፣ ላሊበላ እና ሙጃ አካባቢዎች እንዲሁም በሰሜን ጎንደር በማይጠብሪና አካባቢው ጠላት በከፍተኛ ሁኔታ እሸሸ ስለሆነ የጠላት ቡድን አባላትም ሆኑ አንድም የሕዝብ እና የመንግሥት ሃብት ይዞ እንዳይወጣ ሁሉም በአካባቢው እየተደራጀ የሚሸሸው ቡድን ላይ እርምጃ እንዲወስድ እና አስፈላጊን መረጃ ለጸጥታ አካሉ እንዲሰጥ የአማራ ክልል መንግሥት ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ነሐሴ 30/2013 ዓ.ም